Publications

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፸፫/፪ሺ፲ ዓ.ም የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት (ማሻሻያ) አዋጅ..ገጽ ፲ሺ፫፻፵፫

image description

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፸፫/፪ሺ፲ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ
የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት አዋጅ ቁጥር ፰፻፲፬/፪ሺ፮ የግብይት ተዋናዮች ውስጥ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ሰበሳቢዎችን የማያካትት በመሆኑ በመስኩ ተፈላጊውን ጥራት ማምጣትና ምርትን በአግባቡ መሰብሰብባለመቻሉ አገርንና በዘርፉ ስራ ላይ የተሰማሩትን ዜጎች ጭምር ማግኘት የሚገባቸውን ጠቀሜታ ማስጠበቅ እንዲቻል አዋጁን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው
ታውጇል፡፡