Publications

አዋጅ ቁጥር ፱፻፹/፪ሺ፰ ዓ.ም /Proclamation No.980/2016

image description

አዋጅ ቁጥር ፱፻፹/፪ሺ፰ ዓ.ም
የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ፍትሀዊ፣ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ በማድረግ የንግዱን ማህበረሰብ እና ህብረተሰቡ ከንግዱ ሥርዓት የሚጠብቀውን አገልግሎት እንዲያገኝ የሕግና የአሠራር ክፍተቶችን በመድፈንና እርካታን በማሳደግ በአገሪቱ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚ ውስጥ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ማድረግ በማስፈለጉ፤ የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ አሰጣጥን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ የንግድ ሥርዓቱ ለመረጃ አያያዝ አመቺ እንዲሆን፣ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ለመግታት የሚያስችል፣ ለመንግስት፣ ለህብረተሰብ እና የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ በማስፈለጉ የንግድ ሥርዓቱ ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት በማድረግ የአገሪቱን ራዕይ ለማሳካት እንዲቻል አገሪቱ ዘመናዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ሕግ እንዲኖራት ማድረግ አስፈላጊሆኖ በመገኘቱ፤