የንግድ ምዝገባ ማሻሻያ

የንግድ ምዝገባ ማሻሻያ

image description

 

1 - አጠቃላይ መረጃ

በጠቅላላ መረጃ ቅፅ ላይ በስተግራ የቀደመውን መረጃ እና በቀኝ በኩል የሚደረጉትን ለውጦች ይመለከታሉ ፡፡

በዚህ ቅጽ ካፒታልን እና ዘርፎችን መቀየር ይችላሉ ፡፡

በዚህ ቅጽ ላይ ለውጦችን ማድረግ የማይፈልጉ ከሆነ እለፍ የሚልውን ቁልፍ ተጭነው ወደ አድራሻ ቅጽ መቀጠል ይችላሉ፡፡

የተፈለገውን መረጃ ሁሉ ማስገባቶን ያረጋግጡ ያልተሟላ መረጃ በቀይ ድምቀቱ ላይ ጎላ ተደርጎ ይታያል ፡፡

መረጃውን ከሞላ በኋላ አስቀምጥ ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ። የስኬት መልእክት ካገኙ ቀጥል የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ አድራሻ ወይም ወደ ቅርንጫፍ ቅጽ መቀጠል ይችላሉ ፡፡

2 - አድራሻ

በአድራሻ ቅጽ ውስጥ በመጀመሪያ እርስዎ የሚያዩት የቀዳሚ አድራሻዎች ዝርዝር ነው ፡፡ በዚህ ቅጽ ውስጥ የቀድሞዎቹን አድራሻዎች መሰረዝ ወይም ማረም ይችላሉ ፡፡

ለውጦችን ማድረግ የማይፈልጉ ከሆነ ሁል ጊዜም የአድራሻ ቅፅ እለፍ የሚለውን ቁልፍ ጠቅ በማረግ መቀጠል ይችላሉ ፡፡

አድራሻን ማስተካከል ከፈለጉ በአድራሻው ላይ የእርሳስ ምልክትን ላይ ጠቅ በማድረግ ማስተካከል ይችላሉ፡፡ ሲስተሙ በግራ በኩል ቀድሞያለውን የአድራሻ መረጃ እና በቀኝ በኩል ለውጦችን ማድረግያ ቅፅ ያሳየዎታል ፡፡

በተጨማሪም የመደመር ምልክቱ ያለበትን ቁልፍ በመጫን አዲስ አድራሻ ማከል ይችላሉ ፡፡

የተፈለገውን መረጃ ሁሉ ማስገባቶን ያረጋግጡ፣ ያልተሟላ መረጃ በቀይ ድምቀቱ ላይ ጎላ ተደርጎ ይታያል ፡፡

አድራሻውን ማከል እና ማስተካከል ከጨረሱ ቀጥል የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ሥራ አስኪያጅ ቅጽ መቀጠል ይችላሉ።

ለውጦችን ለማድረግ ወደ ጠቅላላ መረጃ ቅጹ ተመልሰው መሄድ ከፈለጉ ተመለስ የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ፡፡

3 - ስራ አስኪያጅ

በተከታታይ እርሳስ እና መጣያ ቁልፍን ጠቅ በማድረግ ስራ አስኪያጅ ማስተካከል ወይም መሰረዝ ይችላሉ ፡፡

ለግል እና የንግድ እንደራሴ አሁን ያለውን መረጃ ብቻ ማስተካከል ማድረግ ይችላሉ ፣ ለተቀረው የሕግ አቅዋሞች ጨምር የሚለውን ቁልፍ በመጫን አዲስ ሥራ አስኪያጅ ማከል ይችላሉ ፡፡

ሥራ አስኪያጅዎችን ማከል እና ማረም ካጠናቀቁ ወደ መስፈርቶች ቅፅ ለመቀጠል ቀጥል የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ፡፡

ምንም ዓይነት ለውጦችን ማድረግ የማይፈልጉ ከሆነ ቀጣዩን ቁልፍ በመጫን ወደ መስፈርቶች ቅፅ ይሂዱ። እንዲሁም ወደ ቀዳሚው ቅጾች መመለስ ከፈለጉ ተመለስ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማድረግ ይችላሉ ፡፡

4 - መስፈርቶች

በመስፈርቶች ቅጽ ውስጥ ሁሉንም የሚያስፈልጉ ሰነዶችን እንዲጫኑ ይጠየቃሉ።

አስፈላጊ ሰነዶች በቀይ ጽሑፍ የሚል ምልክት ይደረግባቸዋል። አማራጭ ሰነዶችን ላለመስቀል መብት አለዎት ፡፡

ሰነድ ለመስቀል ፣ የቀስት ደመና ቁልፉን ይጫኑ እና ለመስቀል የሚፈልጉትን ሰነድ መምረጥ ያስፈልግዎታል። የሰነድ ጭነት ስኬታማ ከሆነ የስኬት መልእክት ያያሉ ፡፡

ሰነድዎን ከሰቀሉ በኋላ ጨርስ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ጥያቄዎትን መላክ ይችላሉ።

ወደ ስራ አስኪያጅ መመለስ ከፈለጉ ፣ ተመልስ የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ፡፡