Publications

የዜጎች ስምምነት ቻርተር ሰነድ

image description

  1. መግቢያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 67/2012 ህግ የተቋቋመ ቢሮ ሲሆን በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሁለት ዘርፍ ማለትም የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍና የንግድ ግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ተደራጅቶ የሚገኝ ተቋም ሲሆን የከተማው የንግድ ስርዓት ፍትሃዊ እንዲሆንና የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት የጋራ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ያለሰለሰ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

 ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተለያዩ የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ሆኖም የህብረተሰቡን የተሟላ እርካታ ከማስፈን አንፃር በርካታ ያልተወጣናቸው ችግሮችና እጥረቶች እንዳሉ መረዳት ይቻላል፡፡

ስለሆነም ቢሮው የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ ስልቶች ነድፎ የተገልጋዩን ፍላጎት የማርካት ስራ ለመስራት እያንዳንዱ አገልግሎት የሚወስደውን ጊዜ መጠን አውቆ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት የአገልግሎት አይነቱን መለየትና ደንበኞች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታ አዉቀዉ ተገቢዉን አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ይህ የዜጎች የስምምነት ሰነድ በማስፈለጉ የሰነዱን ዓላማዉንና አስፈላጊነቱን እንዲሁም የቢሮውን ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች አካቶ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡