የአድራሻ ለዉጥ
- ማንኛውም ሰው የንግድ ስራው ለማካሄድ ከተመዘገበበትና ከተመደበበት የሥራ ቦታ አከባቢ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ አከባቢ ለመለወጥ ከፈለገ በዚህ ደንብ አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 2 እና 8 ንኡስ አንቀጽ 2 ያደረገውን ምዝገባ መሰረዝና ከወረዳው ጽ/ቤት የተሰጠውን ደረት ላይ የሚንጠለጠል የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ ለወረዳው ጽ/ቤት፤ በቀጣይ መሸኛ ወረቀት በመውስድ ወደመረጠው አከባቢ የሚገኝ የወረዳ ጽ/ቤት መሸኛውን በማቅረብ ሌላ ደረት ላይ የሚንጠለጠል የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ በመውሰድ መነገድ ይችል ፤
- የምዝገባ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ስለማቅረቡ እና ተቀባይነት ስለማግኘቱ የወረዳው ጽ/ቤት ማረጋገጫ መስጠቱንና ተቀባየነት ያገኘበትን ቀን፣ ስለ ምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ በዝርዝር መግለጹን ለአመልካቹ እና ለሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ ይህ የጽሑፍ ማረጋገጫ ካልተሰጠ በስተቀር ያቀረበው የምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ እንደተለወጠ ወይም እንደተሸሻለ አይቆጠርም፡፡