መደበኛ ያልሆነ ንግድ
የጠፋ/የተበላሸ
- መደበኛ ያልሆነ ንግድ ሥራ ምዝገባ ያደረገ ማንኛውም ሰው የተሰጠው የሚንጠለጠል የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ የጠፋበት ወይም የተበላሸበት ከሆነ ቀደም ሲል ለሰጠው የወረዳ ጽ/ቤት በጸሑፍ በማመልከት ምትክ የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ማግኘት ይችላል
- የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ የተበላሸበት ማንኛውም ሰው ምትክ እንዲሰጠው ሲጠይቅ የተበላሸውን ይምልሳል።
- ወረዳው ማመልከቻ ሲቀርብለት ለጠፋው ወይም ለተበላሸው የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያ በዚህ ደንብ የተመለከተውን ክፍያ በማስከፈል ምትክ ፈቃድ ወይም መታውቂያ ይሰጣል።