መደበኛ ያልሆነ ንግድ
የፈቃድ ማሻሻያ
ማንኛውም ሰው ተመዝግቦ የሚሰራውን የንግድ መስክ አይነት መለውጥ ወይም ማሻሻያ ከፈለገ የተመዘገበበት ወረዳ ጽ/ቤት በመቅረብ በቢሮው የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት የሚሰራውን የንግድ መስክ ዓይነት መለወጥ ወይም ማሻሻል ይችላል፡፡
- የምዝገባ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ስለማቅረቡ እና ተቀባይነት ስለማግኘቱ የወረዳው ጽ/ቤት ማረጋገጫ መስጠቱንና ተቀባየነት ያገኘበትን ቀን፣ ስለ ምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ በዝርዝር መግለጹን ለአመልካቹ እና ለሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ ይህ የጽሑፍ ማረጋገጫ ካልተሰጠ በስተቀር ያቀረበው የምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ እንደተለወጠ ወይም እንደተሸሻለ አይቆጠርም፡፡